# started 2014-09-02T08:14:07Z "ሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ከመሬት ከባቢ አየር ውጪ የሚገኙ ክስተቶችን የሚያጠና የሳይንስ ክፍል ነው። ቃሉ አስትሮኖሚ ከግሪክ የመጣ ሲሆን የፀሐይ የከዋክብትና የጨረቃዎች ሕግ ማለት ነው።ሥነ ፈለክ ከጥንታዊ ሳይንሶች አንዱ ነው።"@am . "የሕክምና ታሪክ በኢትዮጵያወቅታዊ ሕዝባዊ ጤና ጉዳዮች በኢትዮጵያ (ደግሞ ትምህርተ፡ጤና ይዩ)ኤችአይቪ/ኤድስ ኢትዮጵያን ለሚጎብኙ የጤና አገልግሎትየመድኃኒትና የህክምና መረጃ በእንግሊዝኛ ያለባቸው ድረ ገጾች"@am . "የሰው ልጅ የሚግባባበት መሳሪያ ነውየቋንቋ ጥናት የሰው ልጅ ልሣናት የሚያጠና ጥናት ወይም ሳይንስ ነው።"@am . "ዋዝንቢት የሦስት አጽቄ አይነት ነው። የፌንጣና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ የረዘሙ አንቴኖችም አሉት።ዋዝንቢት ታዋቂ የሚሆነው በተለይ ስለ ድምጹ ይሆናል። ይህን ለማሰማት የሚችለው አውራ ዋዝንቢት ብቻ ነው፤ የተባዕቱ ክንፍ እንደ \"ሚዶና ሞረድ\" የሚመስል ፍርግርግ መሣሪያ አለበትና። ክንፎቻቸውን በማፋተግ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤ ዘፈናቸውም በየወገናቸው ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን አንስት ይስባልና እጅግ ከፍ ይላል። የመርቢያ ዘፈን አንስቲቱ ስትቀርብ ይጠቅማልና በጣም ቀስ ይላል። አንስት ዋዝንቢት የረዘመ እንደ መርፌም የሚመስል ዕንቁላልም የሚጥል ዕቃ አለባት።በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ወገኖች ይገኛሉ። ዋዝንቢት በሌሊት የሚነቃ ወደ መሆን ያዘንብላል። ብዙ ጊዜ ለዘመዱ ለፌንጣ ይሳታል፣ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ያሉበት የሁለንተናቸው ቅርፅ ተመሳሳይ ነውና።በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል።በእስያ በተላይም በቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ ለማዳ እንስሳ ሆኖ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።"@am . ".ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ ዓ.ም. በአሰላ ከተማ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጂም ርቀት ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ፲ሺ፤ በ፭ሺ፤ በግማሽ ማራቶንና፤ በማራቶን እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሮአል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረ ሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ሺ ሜትር ወርቅ አስመዝግቧል።በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. \"ኤንዱራንስ\" የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ሠርቷል።"@am . "ብርቱካን (ወይም ኦሬንጅ) ማለት የዛፍ አይነትም ሆነ በተለይ የዚሁ ዛፍ ፍሬ ማለት ነው። የሌሎች አትክልት ክልስ ሆኖ ከጥንት እንደ ለማ ይታሥባል። እርዝማኔው እስከ 10 ሜትር ድረስ ቢደርስም ዛፉ ትንሽ ይባላል፤ ቡቃያው እሾህ አለበትና ቅጠሎቹ ከ4 እስከ 10 ሳንቲሜትር ድረስ የሚዘረጉ እንደ ጥድም ወገን መቸም የማይረግፉ ናቸው። የፍሬው መጀመርያ ትውልድ በደቡብ-ምሥራቃዊ እስያ በህንደኬ፣ በቬትናም ወይም በደቡብ ቻይና ተገኘ።"@am . "የድረ ገጽ መረብ (ወይም ኢንተርኔት) በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን ያያየዘ የመገናኛ መረብ ነዉ። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ። ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት «USENET» የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. (1980 እ.ኤ.አ.) አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ጽሑፍ በተገናኙት ኮምፒውተሮች ላይ መልጠፍ የሚፈቅድ ሥርዓት ብቻ እንጂ ስዕል ወይም ሌላ ነገር አልነበረም። መጀመርያው e-mail አድራሳዎች የተሰጡት ከዚያ ዘመን ነው። ዛሬም ብዙዎች ተጠቃሚዎቹ ግን ስንኳ ስለ USENET መኖሩን አያውቁም።መጀመርያው ድረ ገጽ የተፈጠረው በ1983 ዓ.ም. (1990 እ.ኤ.አ.) ሆነ።ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት በመጀመሪያ አገልጋይና (server) ደንበኛ (client) ምን እንደሆኑ ለይተን እንረዳ። አንድ የምግብ ቤት አስተናጋጅ ምግብ ለብዙ ተስተናጋጆች እንደሚያቀርበው፣ ሁሉ ኢንተርኔት ላይ ያለ አገልጋይ (server) የተለያዩ ነገሮችን ደንበኞቹ (clients) ይሰጣል። የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ደንበኞች ይባላሉ ማለት ነው። ደንበኞች የተለያየ ነገር ከአገልጋዩ ሊቀበሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፤ እርስዎ ይህንን ድረ ገጽ ሲመለከቱ የቻሉት አገልጋዩን ድረ ገጹን እንዲልክልዎ በመጠየቅዎ ነው። በመሆኑም ይሄ አገልጋይ «ድረ ገጽ አገልጋይ» (web server) ይባላል። ሌላ አገልጋይ ደሞ መልአክት (email) ሊያቀብል ይችላል። ስለዚህም «መልአክት አገልጋይ» ይባላል።ኢንተርኔት የአገልጋይና የደንበኞች መረብ ነው። በአብዛኛው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ድረ ገጽ (WWW or World Wide Web) ይጠቀማሉ። ስለዚህም ደረ ገጽ የኢንተርኔት ትልቁ ጥቅም ነው። ብዙ ጊዘም ኢንተርኔትና ድረ ገጽ በስህተት አንድ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን መረቡ፤ ማለትም ኢንተርኔት፤ ለሌላ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሰው (USENET) የኢንተርኔት ሌላው ጥቅም ነው።ከአንድ አገልጋይ የሚፈልጉትን ነገር ለመጠያቅ በመጀመሪያ የአገልጋዩን መጥራት ያስፈልጋል። እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩ የሰነድ አድራሻ (URL) አለው። ይሄን የሰነድ አድራሻ በመጠቀም ከየትኛውም ቦታ አገልጋዩን መጥራት ይቻላል። ለምሳሌ www.wikipedia.org የዊኪፒዲያ አገልጋይ የሰነድ አድራሻ ነው። አንዳንዴ አንድ ነገር ፈልገን የትኛው የሰነድ አድራሻ ላይ አንደምናገኘው ላናውቅ እንችላለን። በዚህ ጊዘ ፈላጊዎችን (search engines) እንጠቀማለን። ለምሳሌ www.google.com ላይ የሰነድ አድራሻዎችን መፈለግ ይችላሉ።"@am . "ልዑል ራስ መኮንን የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ።በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ።ልዑል ራስ መኮንን የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓን አገሮች ጎብኝተዋል። በዚህ ጊዜ እሳቸው ኢጣሊያን ሲጎበኙ በነበረ ጊዜ የኢጣሊያ ጋዘጦች የውጫሌ ውልን በተመለከተ፤ «...በውጫሌ ውል ላይ ኢትዮጵያ የኢጣሊያን ጥገኝነት ተቀብላ ውል ከፈረመች በኋላ የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል...» እያሉ የጻፉትን ራስ መኮንን ተቃውሞአቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የውሉን መበላሸት ለአጤ ምኒልክ አሳወቁ። ከኢጣሊያንም ጋር በተደረገውም ጦርነት ራስ መኮንን ፲፭ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ይዘው ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋር ዘምተዋል። በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር ፬ ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር ፱ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ መጋቢት ፲፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ ሰኞ ሚያዝያ ፳፪ ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው። ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ፤-«ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው፤ መኮንን አይደለም ድኃ ነው የሞተው»"@am . "ለፊልሙ፣ አቡጊዳ (ፊልም) ይዩ።አቡጊዳ ማለት ፊደል ነው። ከልሳነ ግዕዝ የተነሣ ነው። ቢሆንም በቅርብ ጊዜ አንዳንድ የፈረንጅ አገር ሊቅ ይህን አባባል ለቋንቋዎች ጥናት ተበድሯል። በዚሁ አነጋገር \"አቡጊዳ\" ማለት በዓለም የሚገኙ ልዩ ልዩ አይነት ጽሕፈቶች ሊያመልከት ይችላል። በየአገሮቹ ፊደላቸው \"አቡጊዳ\" የሚባለው እያንዳንዱ ፊደል ለክፍለ-ቃል ለመወከል ሲሆን ነው እንጂ እንደ እንግሊዝኛ \"አልፋቤት\" ፊደሉ ለ1 ተነባቢ ወይም ለ1 አናባቢ ብቻ ሲሆን አይደለም። ስለዚህ የግዕዙ ፊደል ይሁንና ሌሎችም ለምሳሌ ብዙ የህንድ አገር አጻጻፎች ጨምረው አቡጊዳ በሚለው ስም ይታወቃሉ። ብራህሚክ ወይም ደቫናጋሪ በተባሉት የህንድ አጻጻፎች በኩል እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል በተለየ ፊደል ሲወከል የአናባቢዎች መጠን የሚታየው የፊደሉን መልክ (እንደ ግዕዝ ወይም እንደ አማርኛ) ትንሽ በመቀየሩ ነው። ስለዚህ በቋንቋ ሊቃውንት ዘንድ 'አቡጊዳዎች' ይባላሉ። በተጨማሪ፣ በካናዳ አገር ለጥንታዊ ኗሪ (ቀይ ኢንዲያን የተባሉ) ጐሣዎች ያላቸው አጻጻፍ እንደዚህ አይነት ነው፤ አናባቢው በቅርጹ የሚታየው ፊደሉን በመዞር ወይም በመገልበጥ ነውና። በግእዝ አቡጊዳ ለሚለው የቃሉ መነሻ ከጥንታዊ የሴም ፊደል ተራ የሚለቀመው ነበር። በግሪክም ይህ ፊደል ተራ በ A, Β, Γ, Δ ጀመረ፤ ወይም በስም አልፋ፣ ቤታ፣ ጋማ፣ ዴልታ ናቸው። ይህ ፊደል ተራ በ ሀ ሁ ሂ ሃ በሚል ቅርጽ ማለት በግእዝ፣ በካዕብ፣ በሣልስ፣ በራብእ ውስጥ ገብቶ ሲሰካ፣ አ፣ ቡ፣ ጊ፣ ዳ የሚለውን ፊደል ተራ አስገኘ። ሁሉ በሙሉ የግእዝ አቡጊዳ እንግዲህ እንደሚከተለው ሰንጠረዥ ነው።አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞበ ጉ ዲ ሃ ዌ ዝ ዦገ ዱ ሂ ዋ ዜ ዥ ሖደ ሁ ዊ ዛ ዤ ሕ ጦሀ ዉ ዚ ዣ ሔ ጥ ጮወ ዙ ዢ ሓ ጤ ጭ ዮዘ ዡ ሒ ጣ ጬ ይ ኮዠ ሑ ጢ ጫ ዬ ክ ኾሐ ጡ